ሳላዛት

$27.99

ሳላዛት በ አብርሃም ገነት የተጻፈ፤ ለየት ያለ አፃፃፍ እና ይዘት ያለው አስገራሚ መጽሃፍ ነው ፡ ታግሰው ያንብቡት። መልካም ንባብ!

ከመጽሃፉ የተወሰደ:
"የሀገረዘላለማዊት ካርታ በስንት ጥረት እጄ ሊገባ ችሏል። ካርታው ትንሽ የሚያወዛግብ ነገር አለው።" …..
" የሀገረዘላለማዊትን መዳረሻ የሚያመለክትው የጉዞ መስመር እውነተኛ ነው፣ የጂኦግራፊ ተማሪ ስለሆንሁ በዚህ አልሸወድም። ካርታው የሚገኘው በጣም በጥቂት ሰዎች እጅ ሲሆን የሚዘዋወረው በምስጢር ነው። " …
"ርግጠኛ ተደርጎ የሚወራው እዚች ሀገር እንደምንም የገባ ሰው ለቀጣዩ አንድ ሺህ ዓመት በሕይወት እንደሚኖር ነው።" …..
" ከዚህ ጽሑፍ በታች በዓለም ላይ ባሉ ቋንቋዎች ዐይቼው በማላውቅ የጽሑፍ ፊደል በትንንሹ ሁለት መስመር ጽሑፍ ሰፍሯል። ".....
"ከዛፍና ከቋጥኝ ጋር እየተላተምሁ፣ እየተላላጥሁ፣ እየወደቅሁ፣ እየተነሳሁ አሳሬን እየበላሁ ስጓዝ ድንገት ከፊት ለፊቴ ከየት መጣ ያላልሁት የብርሃን ጎርፍ ከበበኝ። ባለሁበት ፈዝዤ ቆምሁ። ዙሪያዬን ያጥለቀለቀኝ ብርሃን ወደ አንድ ቅርፅ ሰብሰብ አለ። ጨረሩ እንዳይወጋኝ ዐይኔን በእጄ ጋረድ አድርጌ ሳይ የሰው ቅርጽ ያለው ነገር ከፊቴ እንደቆመ ልብ አልሁ። "